በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ ልዑክ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና ጄ. መሐመድ ጋር ወላጆቻቸውን ያጡ እና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍ በሚቻልበት ዙሪያ መከረ
የቻይና የንግድ ሥራ በአፍሪካ ለማህበራዊ ኃላፊነቶች ጥምረት በአፍሪካ ሊገነባ ካቀደው 1 ሺ መንደሮች ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ አስታወቀ
በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቀረጸ ብሔራዊ ስትራቴጂ እቅድ እና የድርጊት መርሀ ግብር ይፋ ሆኗል
previous arrow
next arrow
 

ዜና | News

አዲሱ ሀገራዊ የልማት ፕሮግራም ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን አካታችና ተደራሽ ያደረገ እና ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ሊሆን ይገባል – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

የተባበሩት መንግስታት የስህዝብ ልማት ፈንድ (UNFPA ) ኢትዮጵያ ባዘጋጀው 10ኛው ሀገራዊ የልማት ፕሮግራም ላይ ባለድርሻና አጋር አካላት ምክክር አካሂደዋል። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ...

ሙሉውን አንብብ

የተቋሙ ሰራተኞች በየዘርፉ የተያዙ የልማት እቅዶች እና የተቀመጡ ሀገራዊ አቅጣጫዎች ስኬታማ እንዲሆኑ በላቀ ትጋትና ተነሳሽነት ሊረባረቡ ይገባል

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር ሰራተኞችየተቋሙ ሰራተኞች በየዘርፉ የተያዙ የልማት እቅዶች እና የተቀመጡ ሀገራዊ አቅጣጫዎች ስኬታማ እንዲሆኑ በላቀ ትጋትና ተነሳሽነት ሊረባረቡ እንደሚገባ የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ...

ሙሉውን አንብብ

በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ34ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንደሚሳተፉ ተገለጸ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሰላም እና የትምህርት ሚኒስቴር “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብርን አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ በጋራ ሰጥተዋል። በግለጫው፥ የሴቶችና...

ሙሉውን አንብብ

የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተልዕኮ

በማህበራዊ ዘርፍ

ዜጎች የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት (የአካል ጉዳተኞች እኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ፣ አረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙና ተሳትፎአቸው እንዲጎለብት፣ በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በድህነት ተጋላጭነትና መገለል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎችን) እንዲያገኙ ማድረግ

በሴቶች እና ህፃናት ዘርፍ

ሴቶችን በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤ የህፃናትን መብትና ደህንነት ማስጠበቅ እና የፆታ ዕኩልነትን ማስፈን

ወጣቶች ዘርፍ

ወጣቶች በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ

Follows us on Social Media