|

ጥቃትን የሚጸየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተደራጅቶ መገኘትና በቅንጅት መስራት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል

አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሃገር አቀፍ የማጠቃለያ መርሃ ግብር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ጥቃትን የሚጸየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተደራጅቶ መገኘትና በቅንጅት መስራት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
ሴቶችን በማብቃት ረገድ ብዙ መሰራት ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ በጽኑ እንደሚያምኑ የገለጹት ፕሬዘዳንቷ የተጀመሩትን በርካታ ጥረቶች አንስተው በውጤታማ አፈጻጸም ላይ ለመድረስ በዩንቨርስቲዎቻችን ላይ ከማተኮር ባሻገር በየደረጃው በየአካባቢው የሚገኙ ሴቶች የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል::
አክለውም ይህን ስናሳካ ደግሞ በሙያቸው ስራ ገበያ ላይ ይገኛሉ – በከፍተኛ ሃላፊነት ደረጃዎች ላይ በመገኘት ስኬታማ ውጠት ለማስመዝገብ እንደሚቻል የገለጹት ፕሬዘዳንቷ በሁሉም ዘርፍ ሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የመፍትሔ አካል ለመሆን ተደራጅቶ መገኘትና ቅንጅታዊ ስራዎች ትኩረት ሊያገኙ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *