የዓድዋ ድል – የጥቁር ሕዝቦች የትግል አርማና የመንፈስ ጥንካሬ ምንጭ ሆኖ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል!!

ዓድዋ ኩሩ ሕዝብ እና ነፃ ሀገር ያስረከበን የነጻነትና የድል ሰንደቅ ነው፡፡ ዓድዋ በሁሉም ኢትዮጵያውያ ደምና አጥንት የተገነባ የተጋድሎና የአይበገሬነት ዓርማ ነው፡፡

የዓድዋ ድል አባቶቻችን ለሀገራቸው ክብር ያለአንዳች ልዩነት በጋራ ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ድል ያጎናፀፉን ብቻም ሳይሆን የወል እውነቶቻችንን በጠንካራ አለት ላይ እንዲገነቡ ያደረጉበት ድል ነው፡፡ በመሆኑም ዓድዋ ለእኛ ድልም ቅርስም ነው፡፡ዓድዋ በህብር የጸናች ሀገርን ለመፍጠር መሠረት የጣለና አሁንም የትውልዱ አሻራ ሆኖ የታላቋን ሀገር ትልቅ ስዕል የሚያሳይ የታሪካችን ዋነኛ ምዕራፍ ነው፡፡ ዓድዋ የማይደፈረውን የቅኝ ገዥዎችን የበላይነትና ፍላጎት መና ያደረገ፣ የታሪክ አንጓ ነው። ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት፣ የአፍሪካዊያን የትግል አርማና የመንፈስ ጥንካሬ ምንጭ በመሆኑ አስተሳሳሪ ቅርሳችን ነው፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ እምብርት መገንባቱ ለኢትዮጵያውያን መታሰቢያነት ብቻም ሳይሆን ለነፃነታቸው ለታዋደቁ አፍሪካያን ወንድሞችም ጭምር መሆኑን ያሳያል፡፡  የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባችን፤ የአፍሪካ ድል የሆነውን የዓድዋ ድል የሚዘክር ፕሮጀክት እውን ማድረጓ ያላትን አፍሪካዊ ዕሴት የበለጠ ያጎላዋል።

እናም የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያዊያን ብቻም ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቦች የትግል አርማና የመንፈስ ጥንካሬ ምንጭ ሆኖ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡

ዘጋቢ መላኩ ባዩ

Please follow and like us: