ሁሉም ዜጋ ከሁሉ በፊት ለዘላቂ ሰላም ቅድሚያ ሊሰጥና ዘብ ሊቆም ይገባል!!

ሁሉም ዜጋ ከሁሉ በፊት ለዘላቂ ሰላም ቅድሚያ ሊሰጥና ዘብ ሊቆም ይገባል!!

ለሰው ልጆች ከምግብ፣ መጠለያ እና አልባሳት ባልተናነሰ አስፈላጊ የሆነው ነገር ሰላም ነው፡፡

ግጭት በሚፈጠርበት ወቅት ብዙዎች ከቀያቸው ይፈናቀላሉ፤ ለስደትም ይዳረጋሉ፡፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሰፊው ከመፈጸሙም በላይ ክቡር የሆነው የሰው ህይወት በከንቱ ይቀጠፋል፡፡

ክስተቱ ቢያልፍም እንኳን በተጎጂ ወገኖች ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ በቀላሉ እንደማይሽር ይታወቃል፡፡

በሰፊው ማህበረሰቦችን ዘንድ ለዘመናት በመተሳሰብ፣ በመፈቃቀርና በመቻቻል መንፈስ አብሮ ለመዝለቅ መሰረት የሆኑትን በጎ ማህበራዊ እሴቶች ከመሸርሸር ባለፈ በህዝቦች መካካል መተማመንን ያሳጣል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም፤ ለአመታት በህዝብና በመንግስት ተሳትፎ የተገነቡ የመሠረተ-ልማት አውታሮች ላይም ውድመት ያስከትላል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ በየዘርፉ የምታካሂዳቸውን የልማት እንቅስቃሴዎች በማፋጠን ወደ ሚፈልገው የእድገትና ብልጽግና ከፍታ ላይ ለማድረስና የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስቀመጣቸውን ሰፋፊ ግቦች ያደናቅፋል፡፡ የሀገሪቱን ገጽታም በእጅጉ ያበላሻል፡፡

ምንም እንኳን እነዚህ አሉታዊ ውጤቶች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጎዱ ቢሆንም በተለይ በሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ጫና እጅግ የበረታ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ወቅት በየአካባቢው እየተካሄዱ ያሉ የሰላም መድረኮች ሰላምን ለማስፈን  ለሚደረገው ጥረት ሚናቸው እጅግ የላቀ በመሆኑ የሀገራችን ሴቶችና ወጣቱን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ ከሁሉ በፊት ለዘላቂ ሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥና ዘብ እንዲቆም የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Please follow and like us: