ዛይድ የበጎ አድራጎት እና የሰብአዊነት ድርጅት ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

ድርጅቱ በመጠለያ ለሚገኙ ዜጎች የሚውል የተለያዩ ቁሳቁሶችን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በተገኙበት አስረክቧል።

በሚስተር ያሃያ አልሆሳኒ የተመራ የዛይድ የበጎ አድራጎት እና የሰብአዊነት ድርጅት ልዑክ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም፥ ሚኒስትሯ የኢፌዴሪ መንግስት በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

 

 

ይህንን የመንግስት ጥረት የዛይድ የበጎ አድራጎት እና የሰብአዊነት ድርጅት በቀጣይም እንዲደግፍ የጠየቁት ሚኒስትሯ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ስላደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ አመስግነዋል።

 

 

 

የልዑኩ መሪ ሚስተር ያሃያ አልሆሳኒ ዛይድ የበጎ አድራጎት እና የሰብአዊነት ድርጅት በቀጣይም ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

 

 

 

ዛይድ የበጎ አድራጎት እና የሰብአዊነት ድርጅት በትምህርት፣ በጤናና በተለያዩ በበጎ አድራጎት ስራዎች የሚሳተፍ መቀመጫውን የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ያደረገ ተቋም ነው።

Please follow and like us: