ወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ  ዳይሬክተር ሊላን ዶድዞ እና የወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል ከፍተኛ የስራ አመራሮችን በጽህፈት ቤታቸው ተቀባለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)  ወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው በቀጣይም ከሚንስትር መስሪያቤቱ ጋር በሴቶች በህጻናትና የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሞችን እንዲደግፍ ጠይቀዋል ።

 

 

በወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ  ዳይሬክተር ሊላን ዶድዞ በበኩላቸው ሚነስትር መስሪያቤቱ በተለይም ህፃናትና ሴቶች ላይ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው  በህጻናት ላይ የሚደርሰው  ረሃብና የተመጣጠነ የምግብ  እጥረት ችግር “Enough” ወይንም ይብቃ!   ማስጀመሪያ ላይም በመገኘታቸው አመስግነዋል ። ዳይሬክተሯ አክለውም ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ።

Please follow and like us: