ኢትዮጵያ በአለም የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ በአለም የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈች ነው። “መጪውን ጊዜ አብረን እንጀምር” በሚል መሪ ቃል የአለም ወጣቶች ፌስቲቫል በሩሲያ ሶቺ እየተካሄደ ይገኛል።

በፌስቲቫሉ ከ100 በላይ ሀገራት የተውጣጡ 20 ሺህ ሰዋች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት አስተባባሪነት 70 አባላትን ያካተተ የኢትዮጵያ የልኡክ ቡድንም በፌስቲቫሉ እየተሳተፈ የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ ገልጸዋል።ፌስቲቫሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከአለም ወጣቶች ጋር እንዲተዋወቁ ባህል፣ ታሪክና ተሞክሮ እንዲለዋወጡ ያስቻለ መድረክ ነው ብለዋል።

የአለም ወጣቶች በአንድ መድረክ መሰባሰብ የህዝብ ለህዝብ ትስስርና የባህል ልውውጥን ዕውን ከማድረግ ባሻገር የአለምን ቀጣይ እጣ ፈንታ የመወሰን አቅም እንዳለውም ታምኖበታል።በፌስታቫሉ የተለያዩ ኤግዝቢሽኖች፣ የልምድ ልውውጥና የምክክር መድረኮች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

አጋጣሚውን በመጠቀም የኢትዮጵያን የቡና ስርዓትን ጨምሮ ሌሎች እሴቶችንም ለተቀረው ዓለም በስፋት ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።

ዘጋቢ መላኩ ባዩ

Please follow and like us: