በአለም አቀፍ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ48ኛ ጊዜ የሚከበረዉ ማርች 8 “ሴቶችን እናብቃ ሰላምና ልማት እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በሀገራችን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል። ለመላው የሀገራችን ሴቶች እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!!

እለቱን ምክንያት በማድረግ ቀደም ብሎ በተጀመረው ንቅናቄ ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የአልባሳት ፣የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረግ ተችሏል።

በአሉ በዋናነት የሚከበረዉ በሴቶች ላይ ይደርሰ የነበረዉ ጭቆና ለማዉገዝ ፣ሴቶች በአደባባይ ቆመዉ ሀሳባቸዉ እንዲገልጹ ብቻ ሳይሆን እድል ካገኙ በየትኛዉም የሀገራችን እድገትና ለዉጥ ሊያፋጥኑ በሚችሉ ዘርፎች ከወንድ አጋሮቻችን ጋር በህብረት በእኩል በመሠለፍ በዉጤትና በስነ ምግባር የታጀበ ተግባር መፈጸም እንደሚችሉ ያረጋገጡበትን ሂደት በማውሳት ለቀደምት ሴት ጀግኖች ትልቅ ክብርና ምስጋና የሚቀርብበት ነው።

በዛሬዉ ቀን የማርች 8( ኤይት) በአል ማክበር ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ጽኦታዊ ጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ሴት እናቶቻችንንና እህቶቻችንን የምንረዳበትና የምንደግፍበት እለት ነው።

በተጨማሪም ከሀገራችን የህዝብ ቁጥር 52% የሆኑ ሴቶችን በኢኮኖሚና በልማት ስራዎች የዕኩል ተሳታፊና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የሀገራችንን እድገትና ብልፅግና ለማፋጠን የተጀመሩ ተግባራዊ ምላሾችን የምናጠናክርበ ሊሆን ይገባል::
በዓሉ በየደረጃዉ ሲከበር በበዓሉ ምክንያት የተለያዩ ሰዉ ተኮር ልማታዊ ተግባራት መፈጸማቸዉን ለችግር ለተጋለጡ ሴቶችና ህጻናት ሀብት በማሰባሰብ ድጋፍ ተደርጓል።

<<ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሠላምን እናረጋግጥ!>> መልካም አለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ይሁንልን!🇪🇹💖🙏🏾

ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር

Please follow and like us: