ዓ.ም የሴቶች ቀንን  በዓል አፈፃፀም ግምገማና  የአፍሪካ የህጻናት ቀን በዓል የንቅናቄ እቅድን አስመልክቶ ከሴክተር  መዋቅሮችና አደረጃጀቶች ጋር ተወያየ።

በመድረኩ የማርች 8 እና የዘጠኝ ወር  የእቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ የአፍሪካ ህፃናት ቀን አከባበር ዕቅድ ቀርቦ ክልሎች በቀረቡት  ስራዎች ላይ አስተያየት እንዲሰጡበትና በትግበራ ወቅት በየክልሉ አፈፃፀማቸውን በማየት ተጠናከሮ በሚቀጥሉበትና መሻሻል በሚገባቸው ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂድዋል።

በዕለቱ መድረኩን በይፋ የከፈቱት  በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ  እንደገለፁት ወሩን ለሴቶች ትኩረት ሊሰጥባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ፣የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ፣ዘለቄታዊነትና ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ተግባራት በማስጀመር ለማከበር ታቅዶ ሰፊ ንቅናቄ ስራ መሰራቱንም ሚንስትር ድኤታዋ ገልፀዋል። የ2016ዓ.ም የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በዓልን አስመልክቶም ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ ሃብትን በዓይነትና በገንዘብ በማሰባሰብ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ወደ ቀድሞ ህይወታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

በተጨማሪም የሴት አደረጃጀቶችን በማጠናከር በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ  እንዲሆኑ ማድረግ፣ሴቶች በሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ዙሪያ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ፣ሴቶች በበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ፣የሴቶች ልማት ህብረት ማቋቋምና ማጠናከር ተለይተው የተሰሩ   ዋና ዋና  ተግባራት መሆናቸውም ተጠቅሷል።

አክለውም የአፍሪካ ህጻናት ቀን(ሰኔ 9)  በአገር አቀፍ ደረጃ ማክበር የሚኖረውን ስትራቴጂያዊ ፋይዳ የላቀ መሆኑን በውል በመገንዘብ በዓሉ ስኬታማ ይሆን ዘንድ በተቋም ደረጃ የተቀመጠውን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ያለው ሂደት በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ማካሄድ የሚያስፈልግ በመሆኑ ይህ መድረክ ተጨማሪ ግብአቶች እንደሚገኝበትና እቅድንም የጋራ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልፀዋል ።

Please follow and like us: