383 ለሚሆኑ ሰዎች የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ (Prosthetic orthotics) ሊሰጥ ነው፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከህንድ መንግስትና ኢትጵያ ከሚገኘው የህንድ ኢምባሲ ጋር በመተባበር በአፋር ክልል ለሚገኙ በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው 383 ለሚሆኑ ሰዎች የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ ሊደርግ ነው፡፡

ይህ የተገለፅው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው በኢትጵያ የህንድ አማባሳደር ሚስተር አኒል ኩማር ራኢን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡ሚንስትራ እንደገለጹት ህክምናው በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ሆስፒታል ውስጥ በጥናት ለተለዩ ታካሚዎች ይሠጣል፡፡አክለውም ኢትዮጵያና ህንድ ከዚህ በፊት የተጀመሩ የትምህርት፣ የጤና ፣የኃይልና ኢነርጂ መስኮች የጋራ የትብብር መስኮችን አጠናክሮ ማስቀጠል በሁለቱ ሀገሮች መካከል የቆየውን የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ትስስርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የህንድ አማባሳደር ሚስተር አኒል ኩማር ራኢን በበኩላቸው ሀገራቸው ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘመን የተሻገረ ወዳጅነታቸውን በተለያዩ ዘርፎችም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍን (Prosthetic Aesthetics) ከሚያዚያ 17 ጀምሮ ከ አፋር ክልል ጤና ቢሮ፣ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ከክልሉ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ይሰጣል፡፡

Please follow and like us: