ዜና እረፍት!

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት የተከበሩ ወ/ሮ አለሚቱ አስፋ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ከዚህ አለም በመለየታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል፡፡

የተከበሩ ወ/ሮ አለሚቱ በቀድሞ ቦንኬ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተለያዩ የሥራ መደቦች ባለሙያ፣ የጤና ጽ/ቤት የሰው ሀብት ባለሙያ፣ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የውኃና ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በጋሞ ዞን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ፣ በጋሞ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍና የጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን በአጠቃላይ ለ23 ዓመታት ማገልገላቸውን ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የተከበሩ ወ/ሮ አለሚቱ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የጋሞ ዞን ገረሴ ቦንኬ ምርጫ ክልል ህዝብን በመወከል፤ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል እና የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ሲያገለግሉ ነበር፡፡

በመሆኑም የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በተከበሩ ወ/ሮ አለሚቱ አሰፋ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

 

Please follow and like us: