የሚኒስቴር መ/ቤቱ አጭር መገለጫ

የሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የፌዴራል ተቋም ሲሆን በ2014 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሠረት  ተቋቋመ፡፡ ከ1958 ዓ.ም. ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከዚህ ቀመድ የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርንና የሠራተኛና ማህበራወ ጉዳይ ሚኒሰቴር ተብለው ሲጠሩ የነበሩ ተቋማትን በመዋሃድ የሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር ተብሎ እንዲቋቀቋም ተደርጓል፡፡ ይህ በአዲስ መልክ የተቋቋመው ሚኒስቴር መ/ቤት በስሩ የተለያዩ ዳይሬክተሬቶች የሚገኙ ሲሆን ዋና ዋናዎቹም የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የማህበራዊ ጥበቃ  ማስተባበሪያና መከታተያ ዳይሬክቶሬት፣የአካል ጉዳተኞች ጉዳይዳ ይሬክቶሬት፣ የአረጋውያን ጉዳይ ማስተባበሪያና  መከታተያ ዳይሬክቶሬት ናቸው ፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በአጠቃላይ ከ 350 በላይ በተለያየ የሙያ ደረጃና ዘርፍ የሚገኙ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ከአመራር ስብጥር አኳያ ሚኒስቴር መ/ቤቱን  በሚኒስትርና በሚኒስትር ዴኤታ የሚመሩት ሴቶች ናቸው፡፡  በአጠቃላይ 31 ዳይሬክተሬቶች በሚኒስትር መሥሪያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡