ችግር ፈቺ የፕሮጀክት ድጋፍ ተግባራዊ ማድረግ የዜጎችን ህይወት ለመለወጥ ያስችላል ተባለ

ችግር ፈቺ የድጋፍ ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ በኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመለወጥ ያስችላል ሲሉ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ፡፡ ይህንን የገለጹት ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ሙዳስር ሲዲቁ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነወ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፈዬ ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ሙዳስር ሲዲቁ ጋር በጽህፍተ ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ችግር ፈቺ የድጋፍ ፕሮጀክት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ በኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመለወጥ ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሙዳስር ሲዲቁ በበኩላቸው እንደተናገሩት ፕላን ኢንተርናሽናል ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ እያከናወነች የምትገኘውን የልማት ስራ መደገፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በውይይታቸውም በሚኒስቴር መ/ቤቱና በድርጅቱ መካከል ያለውን ሰትራቴጂካዊ ጥምረት ለማጠናከር እንዲቻል በኢትዮጵያ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ላይ ያተኮረ ሰፊ የድጋፍ ፕሮጀከት ዶክመንት ለማዘጋጀት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *