አለም አቀፍ የሴቶች ቀን “የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በልዩ ልዩ መርሐ-ግብር እየተከበረ ይገኛል

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 “የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በልዩ ልዩ መርሐ-ግብር እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከቀበሌ ጀምሮ እስከ  ዞኖች እና ከተማ መስተዳድሮች በተለያዩ ችግሮች ከቄያቸው የተፈናቀሉ ሴቶችን በመርዳት፣በዝናብ እጥረት ምክንያት የተቸገሩ ሴት አርብቶ አደሮችን  በመርዳት እና ቤት አልባ የሆኑ ሴቶችን ቤት በመስራት እንዲሁም ለታላቁ ህዳሴ ግድባችን ሃብት በማሰባሰብ ተከብሯል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የባህርዳር ከተማ ሴቶችና ህጻናት መምሪያ እንዲሁም ሴት አደረጃጀቶች በጋራ በመሆን ማርች 8 በተለያዮ ዝግጅቶች ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞችን ጋር አክብረዋል።

በዓሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የሴቶች የትምህርት ተሳትፎን ለማጎልበት ከሚሰሩ አካላት ጋር በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

በተመሳሳይ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በሐረሪ ክልል በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን በዓሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ ከንቲባ  ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

በተጨማሪም አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በፌደራል ደረጃ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተላከው መሰረት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *