Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ላይ የሴቶች ተሳትፎና የአመራር ሰጪነት ሚና መጠናከር እንዳለበት ተገለጸ
የአየር ንብረት ለውጥ በሴቶች ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ በመከላከል እንዲሁም የስረአተ ጾታ እኩልነትና ሴቶች በዚህ ሂደት ውስጥ በሚኖራቸው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገው የስልሳ ስድስተኛው የተባበሩት መንግስታት Commission on the Status of Women ስብሰባ በኒውዮርክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሰብሰባው ከመጋቢት 14-25 (እ.አ.አ) ድረስ የስረአተ ጾታ እኩልነትን በማረጋገጥና ሴቶችን በሁሉም መስክ በማብቃት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰትን ከባቢያዊ ጉዳቶችን በተለይም ፖሊሲዎችንና ፕሮግራሞችን ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ መቀነስ ይቻላል በሚል ጭብጥ ነው እየተከናወነ የሚገኘው፡፡
ይህንን አጀንዳ መሰረት በማድረግ በሚኒስትሮች ደረጃ መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በተከናወነው ሰብሰባ ላይ ከኢትዮጵያ አንጻር በቪዲዮ መልእክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት የሴቶችን እምቅ አቅምና እውቀት በማቀናጀት በአየር ንብርት ለውጥ ምክንያት የሚደረሰውን ከባቢያዊ ጉዳት ማስቀረት ያስችላል ያሉ ሲሆን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያየዘ በሴቶችና በአከባቢያቸው ላይ ተግዳሮትን ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን ቅድሚያ ሰጥቶ መመለከት እንደሚገባና ከማህበራዊ አገልግሎቶችና ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አንጸር ያለውን ክፍተት በመድፈን የሴቶችን እኩል መብትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለው እንደተናገሩት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ላይ የሴቶች ተሳትፎና የአመራር ሰጪነት ሚና መጠናከር እንዳለበት የገለጹ ሲሆን የተቀናጀና ሁሉ አቀፍ መረጃ እንዲሁም በቂ እውቀት ለሴቶች ተደራሽ ማድረግም እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ በስብሰባው ላይ አፍሪካን ጨምሮ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በአካል እንዲሁም በቪዲዮ ኮንፍረንስ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
Please follow and like us:
