የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን  ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳወቀ

መጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት UNICEF ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የተሟላ የገንዘበና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የድርጀቱ የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ቀጠናዊ ቢሮ የህጻናት ጥበቃ ሪጅናል አማካሪ አንደሪው በሮክስ ከኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
በውይይታቸው ወቀት ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት መንግስት በተከሰተው ጦርነት እና ድርቅ ምክንያት የተጎዱ አከባቢዎችንና በዚሁ ምከንያት የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ ሴቶችንና ህጻናትን የመደገፍና የማቋቋም ስራን በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ እንደሚገኘ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለው እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር ለረጅም ጊዚያት የቆየና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳለ ገልጸው ይህንን ውጤታማ ገንኙነት ለማጠናከር እንዲቻል በሚኒስቴር መ/ቤቱና በድርጅቱ በኩል የሚከናወኑ ማህበራዊ ድጋፎችን ሳያደራርቡ አቀናጅቶ ለተጎጂዎች ተደራሽ በማድረግ ትክክለኛ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የዩኒሴፍ ሪጅናል አማካሪ አንደሪው ብሮክስ በበኩላቸው እንደገለጹት በቅርቡ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአማራ ክልል ሄደው ማየታቸውንና በዚህ ጦርነት ምክንያት የተፈጠረው ማህበራዊ ችግር ከባድ መሆኑንና በተለይም በክልሉ ጦርነቱ በሴቶችና ህጻናት ላይ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋለ፡፡ የዩኒሴፍ ሪጅናል አማካሪው አክለው እንደተናገሩት በግጭቱና በድርቁ ምከንያት የተጎዱ አከባቢዎችንና የህብረተሰብ ከፍሎችን ለመደገፍና ከዚህ በፊት ከነበረው የላቀ ለማድረግ የተሟላ የድጋፍ አገልግሎትና ቅንጅታዊ ስራዎች በድርጅቱና በመንግስት በኩል ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ዩኒሴፍ በአሁኑ ወቀት በኢትዮጵያ በርካታ ዘርፈ ብዙ የማህበራዊ ድጋፎችን እያከናወነ የሚገኘ ሲሆን በቀጣይም በግጭቱና በድርቁ ምከንያት የተጎዱ አከባቢዎችን የመደገፍ፣በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ለህጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ የማድረግ፣ በህጻናት ድጋፍና ጥበቃ ዙሪያ ተዓማኒ መረጃ እንዲኖር የተደራጀ ሲስተም የመፍጠር፣ በችግር ውስጥ የሚገኙ ህጻናትን ለመደገፍ እንዲቻል የኬዝ ማናጀመንት ስራን የማከናወን እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ባለሙያተኞችን መድቦ የተለያዩ የማህበራዊና የስነልቦናዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ህጻናትና ሴቶች የመስጠት ስራን ለማከናወን ቃል ገብቷል፡፡
በመጨረሻም ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የድርጅቱ ለረጅም ጊዜ የቆየ ያልቶቀጠበ ድጋፍና ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት አድንቀው በቀጣይም ድርጅቱ ያለውን ከፍተኛ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ድጋፍ በተለይም በጦርነትና በድርቅ ምክንያት የተጎዱ አከባቢዎችን ለመደገፍና የረጅም ጊዜ የጋራ ዓላማን ለማሳካት እንዲቻል ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
UNICEF expressed its commitment to continue its full technical and financial support to Ethiopia
March 18, 2022 Addis Ababa – UNICEF expressed its commitment to continue its full technical and financial support to Ethiopia, said by Andrew Brooks, UNICEF Child Protection Regional Advisor for Eastern and Southern Africa Regional Office while discussed with H.E Ergogie Tesfaye (PhD) Minister of the FDRE Ministry of Women and Social Affairs.
During the discussion, H.E Ergogie Tesfaye (PhD) briefly explained that the government has been working rigorously to support internally displaced people (IDP), women and children in the conflict and drought affected areas of Ethiopia. She also added that UNICEF has long standing bilateral relationship with Ethiopia in various social issues and need to pull all efforts together to avoid duplication of efforts to bring a real change in the life of the vulnerable people.
Mr. Andrew Brooks on his part expressed his recent visits of the conflict affected areas of Amhara region and shared his feelings on the magnitude of the problem that affected grimly children and women. He also stated that strong and coordinated work are needed from the government side and international partner organizations to scaleup the joint efforts and to deliver more services in the conflict and drought affected areas.
UNICEF is currently undertaking various multifaceted social supports in Ethiopia and also willing to continue its support especially in the areas like in drought and conflict affected areas, cash transfer to economically disadvantageous people, nutritional support to children and women, strengthening the robust system building for child protection system to have reliable data, establishing child case management and mobilizing a big social work force to give efficient psycho-social service vulnerable people.
Finally, H.E Dr. Ergogie appreciated the long standing, unreserved support and partnership of UNICEF with Ethiopia and urged to continue their much higher technical and financial support to address the recent challenges of conflict and drought as well as the long-term common objective between the government and UNICEF.
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *