Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ዓለም አቀፍ አጋር የልማት ተቋማትበኢትዮጵያ የስርዓት ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
በመርሃግብሩ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት መንግስት የስርዓት ጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ ለኢትዮጵያ ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ወደ ብልጽግና የሚያደርሰውን የአስር ዓመቱን የልማት ዕቅድ በማቀድ ወደ ትግበራ መገባቱን የገለጹ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደ ተቋም የ10 ዓመት እቅድ በማዘጋጀት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን በማለት ለዓለም አቀፍ አጋር የልማት ተቋማት ተወካዮች አብራርተዋል∶∶

በኢትዮጵያ የሰፔን አምባሳደር ማኑኤል ሳላዛር በበኩላቸው የስርዓት ጾታ እኩልነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ እያደረገች ላለችው ጥረት ያላቸውን አድናቆት ገልጸው መሰረታዊ ናቸው ያሏቸውን ማለትም የፖሊሲ ጉዳዮች፣ ጥምረትና የትግበራ ስራ ትኩረት የሚፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን እንደ ከዚህ ቀደሙ የሴቶችንና የልጃገረዶችን ህይወት በሚቀይር መልኩ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰሩና አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል∶∶

ክብርት ሚኒስትሯ በበኩላቸው እንደገለጹት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ የሚሹ ሴቶችና ልጃገረዶችን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ለማገዝ የሚረዳ ተቋማዊ እቅድ በማዘጋጀት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረው የተጀመረው የትብብር ስራ ፍሬ አፍርቶ ውጤት እንዲያስመዘግብ ድጋፍ እያደረጉ ላሉ አጋር አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል ∶∶
በኢትዮጵያ የስርዓት ጾታ እኩልነት ለማረጋገጥ ከመስራት ባሻገር በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በችግር ውስጥ የሚገኙትን ዜጎች መርዳት እና በቀጣይ ሊካሄድ በታሰበው ብሄራዊ ውይይት የሴቶችን ተሳታፊነት ማሳደግ ላይ ዓለም አቀፍ አጋር የልማት ተቋማት እና ሚኒስቴር መ/ቤቱ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ∶∶
Please follow and like us:
