ቤተሰብ ተኮር ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች ለዘላቂ የልማት ግቦችና ለሀገራዊ የልማት እቅዶች መሳካት ከፍ ያለ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡

የቤተሰብን የህብረተሰብ መሰረትነት ሚናውን ማስቀጠልን አስመልክቶ በአዳማ ከተማ ሀገራዊ የምክክር መድረክ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
ቤተሰብ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ እድግት ወሳኝ ሚና ከሚወጡ ማህበራዊ ተቋማት ውስጥ ዋነኛው መሆኑና ቤተሰብ ተኮር ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች ለዘላቂ የልማት ግቦችና ለሀገራዊ የልማት እቅዶች መሳካት ከፍ ያለ ሚና እንዳላቸው ተገልጸዋል፡፡
የምክክር መድረኩን ያስጀመሩት የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት የሀገር ዋልታ መሰረቱ ቤተሰብ እንደመሆኑ መጠን በተለይ ህጻናትን በማነጽ መልካም እሴቶችን በማስረጽና በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ የቤተሰብ አባላትን በማረጋጋት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ጉልህ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለው እንደገለጹት የቤተሰብ ሚና በኢትዮጵያ ለሀገር እድገት ብሎም ትውልድን በተሳካ ሁኔታ በማነጽ ረገድ ያለው አበርክቶ እጅግ ከፍተኛ መሆኑና በተለይ ለሀገራችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በእለቱ የቤተሰብ ተቋምን ለማጠናከር የተወሰዱ እርምጃዎችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ በአቶ ዳምጠው አለሙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአረጋዊያን ጉዳይ ማስተባበሪያና መከታተያ ዳይሬክተር ሰፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡
በኢትዮጵያ የቤተሰብ ተቋማዊ ገጽታዎች እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲሁም የአለም አቀፍ ተሞክሮን በተመለከተ የጂማ ዩኒቨርስቲ የሶሲዮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር በሆኑት አቶ ነጋ ጅባት ገለጻ ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይ የህብረተሰብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለውን የቤተሰበ ህጋዊ ጥበቃን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመጡ መምህርና የህግ አማካሪ በዶ/ር ዮናስ ቢርመታ የውይይት ጽሁፍ ቀርቦ በዕለቱ በተገኙ ተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *