ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ለመቀበል የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች

ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ለመቀበል የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቅን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ አመራሮች ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን በግዚያዊነት ማረፊያ እንዲሆን በተለምዶ ወሰን ሁለት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኘው የመንግስት ከስደት ተመላሾች ጊዜያዊ ማቆያ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በመገኘት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ አመራሮች ከስደት ተመላሾችን ለመቀበል የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡
ከነገ ረቡዕ መጋቢት 30 ቀን 2022 ዓ.ም ጀምሮ በመጪዎቹ 7-11 ወራት ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንደሚመለሱና መልሶ የማቋቋም ስራዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ ስራዎች ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *