የሀዘን መግለጫ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽንን ላለፉት አመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩ የነበሩት ወ/ሮ ወይንሸት ሙሉሰው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽንን ላለፉት አመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩ የነበሩት ወ/ሮ ወይንሸት ሙሉሰው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ፣ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት (9፡00) ላይ የካ ሚካኤል በሚገኘው ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በመሆኑም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በወ/ሮ ወይንሸት ሙሉሰው ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናት ከልብ ይመኛል፡፡
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን!!

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *