የመገናኛ ብዙሃን ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና በሰዎች የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል የመገናኛ ብዙሃን ሚና የጎላ ነው ተባለ

የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣውን ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና በሰዎች የመነገድ ወንጀል ለመከላከል ከፍተኛ ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተገልጿል።

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና በሰዎች የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል የመገናኛ ብዙሃን ሚና ላይ ያተኮረ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አውደ ጥናት ተካሄደ።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በፍሪደም ፈንድና በአጋሮች በተዘጋጀው መድረክ የሚዲያ ተቋማት ማህበረሰቡ ስለጉዳዩ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ሊረባረቡ ይገባል ተብሏል።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መያድ ገር በመሆን በሰዎች የመነገድና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ለመከላከል በትኩረት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከ133 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ አገር ቤት በመመለስ የማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ድጋፍና ወደ መህበረሰቡ የመመለስና የማቀላቀል ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የሚዲያ ተቋማትም የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል፣ በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለማህበረሰቡ የማድረስ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከታተያ የተመላሽ ዜጎች ክትትልና ድጋፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግ ይበሉ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የተመለከቱ የአገር ውስጥና የውጪ አገራት የህግ ማዕቀፎችን አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የመገኝበትን ሁኔታ እና በመንግስትና በአጋሮች እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችና ጥናታዊ ፅሑፎች ለሚዲያ ተቋማት ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል ።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *