የቤጂንግ መግለጫ እና የድርጊት መርሀግብር 30ኛ ዓመት አህጉር አቀፍ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።

ውይይቱ አፍሪካ በአለም አቀፍ ደረጃ በሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና በሴቶች ልማት ላይ ትኩረት ያደረገና CONVENSION ON THE STATUS OF WOMEN (CSW) ላይ የአፍሪካን ሪፖርት ለማጠናከርና ግብአት ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ለመሰብሰብ ያለመ ነው።

በውይይቱ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን አንደገለፁት በያዝነው በጀት ዓመት የቤጂንግ 30ኛ ዓመት በማስመልከት ኢትዮጵያዊ ሀገር አቀፍ ግምገማና የሪፖርት ዝግጅትን ያከናወነች መሆኑን አስታውሰው ይህንንም አህጉር አቀፍ ውይይት ኢትዮጵያ ማስተናገዷ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያርገው ገልፀዋል ። ሚኒስትር ድኤታዋ እንደገለፁት የቤጂንግ መግለጫ እና የድርጊት መርሀግብር ባለፉት አምስት ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ ግምገማ ያደረግን ሲሆን ይህ አህጉራዊ ግምገማም ድሎችን፣ ተግዳሮቶችን እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ከግብ ጋር በጋራ ለማየት እንደሚያስችል ተጠቅሷል።

አክለውም የድርጊት መርሀግብሩን ትግበራ ማፋጠን እና ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የሴቶችን የአመራር ቦታ ውክልና ማሳደግ፣የታዳጊ ሴቶችን የትምህርት ተደራሽነት መሻሻል እና የሴቶችን መብት ለማስጠበቅ የተሻሻሉ የህግ ማዕቀፎችን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች አመርቂ መሻሻል መታየታቸውን ገልፀዋል ። በተጨማሪም የእናቶችን ጤና ለማሻሻል በተደረገው ጥረት የእናቶች ሞት መጠን በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም በማጎልበት ረገድም እና መሬትን ጨምሮ ምርታማ ሀብቶችን ለማግኘት የተጀመሩ ጅምሮች ለሴቶች የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ውጤት አንዳስገኘ ጠቅሰዋል ። ነገር ግን አሁንም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን፣ ኢኮኖሚያዊ እኩልነትን እና የሴቶችን በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ሙሉ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን መፍታት መቀጠል ላይ በትኩረት ለመስራት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ይህ የባለሙያዎች ውይይቶች የቤጂንግ+30 አፍሪካ የትንታኔ ግምገማ ግኝቶቹ ለአፍሪካውያን ሴቶች ምን ማለት እንደሆነ ፣በ69ኛው የሴቶች ሁኔታ ኮሚሽን ላይ እንደ አህጉር የምናስተላልፋቸውን ቁልፍ መልእክቶች በመቅረፅ በጥልቀት ለመገምገም እንደሚያግዝ ይታመናል። በአለም አቀፍ ደረጃ በሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና በሴቶች ልማት ላይ ትኩረት ያደረገና CONVENSION ON THE STATUS OF WOMEN (CSW) በመባል የሚታወቀው ዋና ዓለም አቀፍ ፖሊሲ አውጪዎች የሚሳተፉበት የጉባኤ መድረክ በየአመቱ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡

 

Please follow and like us: