ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች የተሻለ ተጠቃሚነት ብሎም ለቤተሰብ መልካም እሴት ግንባታ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል

በአረጋውያንና ቤተሰብ ጉዳይ እንዲሁም በአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላትን ግንዛቤና ምላሽ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ ያለመ የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ እሸቱ በአለማችንም ሆነ በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት እያጋጠሙ ባሉ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ክስተቶች ምክንያቶች የቤተሰብ፣ የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞች ደህንነት አደጋ ላይ የሚወድቅበትና ለችግር የሚጋለጡበት ሁኔታ ይስተዋላል። የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞችን መብት የማስከበር ፣ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥ ብሎም የቤተሰብን መልካም እሴት የመገንባት ጉዳይ ያለሰለሰ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

እስካሁን እንደሀገር ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራትና ውጤታማ በማድረግ ረገድ አበረታች ጅማሮዎች ቢኖሩም በዘርፉ የሚፈለገው ለውጥ እንዲመዘገብ በቅንጅት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም ጉዳዩን በባለቤትነት እና በኃላፊነት መያዝ፣ አዎንታዊ አመለካከትና የጠራ ግንዛቤ ማዳበር እንዲሁም ለተጨባጭ ለውጥ በቁርጠኝነት መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በመድረኩ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር ቢሮ የስራ ኋላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በየዘርፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች በኩል ልዩ ልዩ ሰነዶች ቀርበው ግንዛቤ እንዲያዝባቸው ተደርጓል።

 

Please follow and like us: