የሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር ከዴቨሎፕመንት ኤክስፐርት ሴንተር (DEC) የጋራ የስራ ስምምነት አደረገ።

የሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር ከዴቨሎፕመንት ኤክስፐርት ሴንተር (DEC) ከፍልሰት ተመላሽ ሴቶችና ታሳቢ ፍልሰተኞች ላይ ያተኮረ የጋራ የስራ ስምምነት አደረገ።

በስምምነት ስነስርዐቱ ላይ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ አንደገለፁት መንግስት መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ለመግታት የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል ::!

ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች፣ የፍልሰት ተመላሾችን፣ታሳቢ ፍልሰተኞች፣ የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጎጂ ሴቶችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም እንደሚረዳ ጠቁመዋል ።

ፕሮጀክቱ በዋናነት ከፍልሰት ተመላሽ ሴቶችና ታሳቢ ፍልሰተኞችን ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመቀየር የዕውቀትና ክህሎት ስልጠናን ጨምሮ የአቅም ግንባታ በመስጠት ወደ ስራ መግባት እንዲችሉ ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል።

ከዴቨሎፕመንት ኤክስፐርት ሴንተር (DEC) ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሀኑ ደምሴ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ለአንድ ዓመት ተኩል የሚቆይ ሲሆን በዋናነት በሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ወሎ፣ በወልድያ እና በደሴ ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 1500 ከፍልሰት ተመላሽ ሴቶችና ታሳቢ ፍልሰተኞች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል።g

Please follow and like us: