በሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር የሚመራው በግጭት ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ምላሽ መስጠትና መልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ላይ ውይይት ተደረገ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር ) በበኩላቸው እንዳሉት በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ችግር ዋና ተጠቂ የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህ አይነቱ ፕሮጀክትም ሴቶችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ማህበረሰቡን እንደሚያግዝም ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ በፌደራል በክልል እና በወረዳ ደረጃ ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት መስራትና ጠንካራ አጋርነት መፍጠር ለአፈፃፀሙ ውጤት አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል ። የፕሮጀክቱ ዓላማዎች ለፆታዊ ጥቃት ምላሽ አገልግሎት መስጫዎችን ተደራሽ ማድረግና ማስፋፋት፣ ጾታዊ ጥቃትን መከላከልና የባህሪ ለውጥ ማምጣት፣ ተቋማት
ፆታዊ ጥቃትን በሚመለከት የሚያከናውናቸውን ተግባራት የማስተባበር ፣ ፓሊሲዎችን የማዳበር እና ፆታዊ ጥቃትን የሚመለከቱ ጥናቶችን መደገፍ ነው። በ2015 እና 2016 በፕሮጀክቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በስጋት ቅነሳ መከላከል እና የባህሪ ለውጥ ስልጠና፣ ስነልቦናዊ ማህበራዊ ድጋፍ ፣ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ድጋፎች፣ የፊስቱላ እና የፔልቪክ ኦርጋን ፕሮፕላስ ህክምናዎች፣ የገቢ ማስገኛ ስልጠናዎችን መስጠት ፣የመልሶ ማቋቋሚያ እና የስራ ማስጀመሪያ ቁሳቁስ መስጠት በዋናነት እንደሚገኙ በመድረኩ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ በአፋርና፣በአማራ፣በቤንሻንጉል-ገሙዝ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች በግጭት ምክንያት ለተፈጠሩ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን ድጋፍ ለመስጠት ያለመ የመንግስት ፕሮጀክት ነው።

Please follow and like us: