Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የከተማ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ስኬቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የከተማ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ስኬቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ከባለድርሻ አካላትና ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ።
በውይይቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የከተማ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ከአለም ባንክ የተገኘውን ውስን ሃብት በማቀናጀት ለችግር የተጋለጡ ቤተሰቦች በ20 ከተሞች ተለይተው በአገልግሎት ሰጪዎች አማካይነት እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ የከተማ ሴፍቲኔትና ስራፕሮጀክት መስሪያ ቤቱ የክልልና የከተማ አስተዳደሮችን በማስተባበር የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ከሚያገኙት ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በማህበራዊ ሰራተኞች አማካኝነት በሚደረግ የቤት ለቤት ጉብኝትና ኬዝ ማኔጅመንት የመሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ፍላጎት መግለጫ መረጃዎች በመታገዝ የእህል እና የአይነት ድጋፎችን በመስጠት በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ጠቅሰዋል ። እ.ኤ.አ. በ 2021 የተካሄደው ስትራቴጂያዊ ለውጥ ፈጣን ዕርዳታን አልፈው ወደ ተቀናጀ እና ዘላቂነት ያለው ሞዴል የሰብአዊ ርዳታዎችን ከረጅም ጊዜ ልማት ጋር በማገናኘት በከተሞች ድህነትን በመዋጋት ዘላቂ ለውጥን ለማምጣት አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።

የፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ማንዋሉ ባስቀመጠው መሰረት ለተጠቃሚዎቻችን አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የተሰጠንን ትልቅ ተቋማዊ ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንድንችል በዓመታዊ እቅዳችን በማካተት ከምናደርጋቸው የአቅም ግንባታ፣ የድጋፍና ክትትል ስራዎች በተጨማሪ ሴክተራችንን ጨምሮ ስራው በቀጥታ ከሚመለከታቸው ፈፃሚ ተቋማት ጋር በመሆን ሚኒሰቴር መስሪያቤቱ እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ። በዚህ ፕሮጀክት በተጨማሪነትም ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ በርካታ ዜጎች ከጎዳና ላይ ተነስተው በማቋቋሚያ ማዕከላት ከመሰረታዊ የምግብ፣ መጠለያና አልባሳት አቅርቦት ባሻገር የስብዕና ግንባታ እና የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን በመውሰድ ከቤተሰብና ማህበረሰብ ጋር በመቀላቀልና በመዋሃድ ከነበሩበት አስከፊ ህይወት እንዲላቀቁና የመጨረሻው አላማ የሆነውን በዘላቂነት ማቋቋም የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንደሆነ ገልፀዋል ።
፨
