የብሔራዊ እና ክልላዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረቶች የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ

ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የብሔራዊ እና ክልላዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረቶች የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

የግምገማ መድረኩ በሁለተኛ ቀን ውሎው የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ሪፖርት ላይ የታዩ ክፍተቶችና የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም ብሔራዊ የቅብብሎሽ ሥርዓት መልካምና ፈታኝ ሁኔታዎች እና ለግዳጅ ወንጀለኛነት የሚፈፀም በሰው መነገድ ወንጀል በተመለከተ የዳሰሳ ፅሁፎች ቀርበዋል።

በቀረቡ ፅሁፎች ላይ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ እና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሁሪያ አሊ የመድረክ አወያይነት ውይይት የተደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች እንዲሁም ጥያቆዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። በመጨረሻም ጥምረቱን የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎች ላይ በየደረጃው ሊሰሩ ስለሚገባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ብሎም የአቅም ግንባታ ስልጠና ስራዎችን በተመለከተ፣ የፍልሰት ተመላሾችን ከመቀበል እና መልሶ ከማቋቋም ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያሉ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

ለዚህም ብሔራዊ የቅብብሎሽ ስርዓቱን በደንብ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚስፈልግ እንዲሁም ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ቀርበው ውሳኔና አቅጣጫ እንዲሠጥባቸው የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ለይቶ ማቅረብ እንደሚገባ በማሳሰብ እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማመላከት የግምገማ መድረኩ መጠናቀቁን ፍትህ ሚኒስቴር እስታውቋል።

 

Please follow and like us: