Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶች እኩልነት ባህል እስከሚሆን ድረስ ጥረታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር የዋለው የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በሸገር ከተማ በተዘጋጀው የማጠቃለያ መርሃ-ግብር መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የሴቶች እኩልነት ባህል እስከሚሆን ድረስ ጥረታችንን
አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሴቶችን በማብቃት ረገድ የተገኙ ውጤቶችን እውቅና ለመስጠት፣ ላገጠሙ ተግዳሮቶች በቅንጅት በመወያየት መፍትሄ ለማመላከት በዓሉ እንደሚረዳ ተናግረዋል። የዚህን አመት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢ እንዲስፋፉ ለማድረግ እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን ድርሻ በመውሰድ ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ ለማብቃት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

የዚህን አመት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ስናከብር ከወትሮው በተለየ ከአዳራሽ ወጣ ባለ መንገድ በአካል ከማህበረሰቡ ጋር በመገኘት በተጨማሪ የሀገራችን ሴቶችን ፍላጎቶችና አንገብጋቢ ችግሮች ከራሳቸው ለማዳመጥ እድል የፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል። በዕለቱ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላሰመዘገቡ ሴት ተማሪዎች (7ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ክፍል)፣ በግብርናው መስክና በኢንቨስትመንት ዘርፉ ለተሻለ ውጤት ለተጉ ሴት ኢንቨስተሮች ፣ ዕውቅናና ምስጋና ዋንጫና ሠርተፍኬት በመስጠት ተጠናቋል።
