Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የፌዴራል ከፍተኛ ሴት አመራሮች በሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ ከሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር ተወያዩ
የፌዴራል ከፍተኛ ሴት አመራሮች ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ጋር በሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። ውይይቱ በዋናነት በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች በተለይም በጤና፣ በጎልማሶች ትምህርት እንዲሁም በገቢ ማስገኛ ለተሰማሩ ሴቶች በቂ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ የተጀመሩትን ውጤታማ ስራዎች የበለጠ አጠናክሮ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በሰፊው መክረዋል።

በተጨማሪም የክልሉ ሴቶችን በአመራርነትና ውሳኔ ሰጪነት ረገድ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንዳለበት የጋራ መግባባት ተደርሷል። አለም አቀፉ የሴቶች ቀን ማርች 8 የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ ሴት አመራሮች በተገኙበት በመስክ ጉብኝትና በውይይት ተከብሯል
Please follow and like us:
