Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሳውዲ መንግስት 50 ቶን ቴምር ለኢትዮጵያ በስጦታ አበረከተ።
የሳውዲ መንግስት በአገሪቱ ለሚገኙ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል 50 ቶን ቴምር በሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል።

ሚኒስቴሩ ከሳውዲ መንግስት የተረከባቸው ቴምሮች የተለያዩ ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ እንዲውል ታስቦ እንደሆነ በዕለቱ ርክክብ ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ አስታውቀዋል ።

ሚኒስቴሩ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶ ጋር በመተባበር ሀብት በማሰባሰብ የማህበራዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተደራሽ የማድረግ ስራ እየሠራመሆኑን ገልፀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው የሳውዲ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትንም የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰዋል።
Please follow and like us:
