Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሁሉን አቀፍ ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳን የያዘ የተጠቃለለ ህግን በማጠናቀቅ በአፋጣኝ ወደ ተግባር ማስገባት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
ፆታዊ ጥቃት ከጊዜ ወደጊዜ መልኩንና አይነቱን ውስብስብ በሆነበት በአዲሱ የአለም ስርዓት ሁሉን አቀፍ ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳን የያዘ የተጠቃለለ ህግ እንደሚያስፈልግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ፣ማህበራዊ ልማት፣ባህልና ስፓርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ ገልፀዋል።

ሁሉን አቀፍ ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳ ሰፊ በሆነው ፆታን መሰረት ባደረገ ጥቃት ውስጥ የሚካተት በተለያዩ የአፈጻጸም መንገዶች የሚፈጸም እንደአካላዊ፣ ስነልቦናዊና ማህበራዊጉ ዳቶችን በተጎጂው ላይ የሚያስከትል መሆኑን አውስተዋል። በተጨማሪም ሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፣ የቤት ውስጥ ጥቃትን፣ ሴትን መግደልን፣ እና ከንብረት ብዝበዛ እና
የመሬት ግጭቶችን ጨምሮ የአካባቢ ጥቃትን ለመፍታት እርምጃዎችን እንዲወስዱ የህጉ በአስቸኳይ መፅደቅ አስፈላጊ መሆኑንና ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቴ በበኩላቸው ድርጊቱ ወንጀል ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከመንገድ ላይ ለከፋ እስከ አካለዊ ጥቃት፣ ከስነልቦና ጫና እስከ አካልጉዳት እና ሞት ሊያስከትል የሚችልና በየትኛውም እድሜ፣ ጾታ እና ሁኔታ ባለ ሰው ላይ ሊደርስ የሚችል ድርጊት በመሆኑ ሁሉም ሰው ይህን ድርጊት መፀየፍ አለበት ሲሉ ተደምጠዋል።

የውይይይቱ ተሣታፊዎች እንደገለፁት ፆታን እና ወሲባዊ ጥቃቶችን መሰረት ያደረገ ወጥ ህግ አለመኖሩ፣በዚህ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ግለሰቦች ላይ የሚወሰደው የህግ አርምጃ በቂ እና አስተማሪ አለመሆኑ እንዲሁም ደግሞ በተለያዩ ህጎች የሚገኙ ጾታዊ እና ወሲባዊ ጥቃቶችን የሚመለከቱ አንቀጾች በተለያዩ መልኩ ሊፈጸሙ የሚችሉ ወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃቶቸን በበቂ መልኩ አለመሸፈናቸውን ለችግሩ መስፋፋት ምክንያት መሆኑን አንስተዋል። በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱትን ጥቃቶች አጽንኦት
በመስጠት እነዚህን ጉዳዮች በሕግ፣ በፖሊሲ እና
በተግባር ለመፍታት እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ
ቀርቧል።
