Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
3 ሺህ 374 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 374 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ 3ሺህ 337 ወንዶች እና 35 ሴቶች እና 2 ጨቅላ ህፃናት የተመለሱት ሲሆን ከእነዚህ መካከል 39 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ወዲህ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 25 ሺህ 583 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ ይገኛል፡፡
Please follow and like us:
