3 ሺህ 352 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 352 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 996 ወንዶች እና 347 ሴቶች እና 9 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 65 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 32 ሺህ 354 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

 

Please follow and like us: