Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የአካል ጉዳተኞችና የአረጋዊያን ማህበራትን ማጠናከርና ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት እንደሚገባ ተገለፀ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለክልል የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ አመራሮች፤ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋዊያን ማህበራት አመራሮች የአቅም ግንባታ ሰልጠና ሰጥቷል።

የአረጋውያንና ቤተሰብ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሮበሌ እንደገለፁት የአካል ጉዳተኞችና የአረጋዊያን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸው ከማረጋገጥ አንጻር የክልል የማህበራዊ ዘርፍ አመራሮች እና የአካል ጉዳተኞችና የአረጋዊያን ማህበራት እና አባላቶቻቸውን መደገፍና ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰዋል። ለዚህም የአመራሩ ድርሻው የጎላ በመሆኑ የአካል ጉዳተኞችና የአራጋዊያን ማህበራትና የክልል የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊዎችን በፕሮጀክት ቀረጻና በሀብት አሰባሰብ፤ በአመራርነት ሚና፤ በመረጃ አያያዝ (MIS) ስልጠና ለመስጠት ሚኒስቴር መ/ቤቱ መድረኩን ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።

የአካል ጉዳተኞች መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ሲሳይ ጥላሁን በበኩላቸው ዓለማውም የክልል የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊዎች፤ የአካል ጉዳተኞችና የአረጋዊያን ማህበራት አመራሮችን አቅም በማሳደግ እና የመፈጸም አቅማቸው ከማጎልበት በተጨማሪ በዘርፍ ደረጃ ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር እንደሚረዳ ጠቁመዋል።

በዚህም የአካል ጉዳተኞችን የእኩል ዕድል ተጠቃሚነት ለማሳደግ፤ የአረጋዊያን መብቶች እንዲከበሩ እና የቤተሰብ ደህንነት እንዲጠበቅ ለማስቻል እና ማህበራቱም በውይይት ሂደት እንዲማማሩ ልምድ እንዲላዋወጡ እንዲሁም የራሱን መብትና ጥቅም በትክክል ሊያሰከብር የሚችል ጠንከራ ማህበራት ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።
