3 ሺህ 528 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 528 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 3236 ወንዶች እና 276 ሴቶች እና 16 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 88 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። በ4ኛው ዙር በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 42 ሺህ 924 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

Please follow and like us: