በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የማስፈፀሚያ ማንዋሎች ላይ ለአስፈፃሚ አካላት አቅም ግንባታ ስልጠና እየተሠጠ ነው

በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የማስፈፀሚያ ማንዋሎች ላይ የአስፈፃሚ አካላት አቅም ለማጎልበት ያለመ ስልጠና እየተሠጠ ነው።

በመድረኩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ጥበቃ ማስተባበሪያና መከታተያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ቴዎድሮስ ሹመቴ እንደገለፁት በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ለዜጎች የሚሰጡ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ አገልግሎቶች የተጠቃሚዎች መብትና ሰብዓዊ ክብር የሚያስጠብቁ ሊሆኑ ይገባል። ከክልል ጀምሮ በየደረጃው በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ሲያደርጉ የትግበራ ስርዓቶችንና እውቀትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ጨምረው ገልፀዋል።

በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ዓይነት የስነልቦናና ማህበራዊ ችግር ያጋጥማቸዋል? የአእምሮ ጭንቀቶች መንስኤያቸው ምንድናቸው? ለነዚህ ችግሮች የምክር አገልግሎት ለመስጠት መርሆዎቹ ምንድናቸው? በሚሉት ዋና ዋና ሀሳቦች ላይ ስልጠናው ያተኮረ በመሆኑ ለስራቸው ውጤታማነት የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ብለዋል። ለዚህም ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት በአግባቡ በስራ ላይ እንዲያውሉም አሳስበዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለፕሮጀክቱ ስኬታማ ትግበራ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

Please follow and like us: