ሚኒስቴሩ ለቀዳማይ ልጅነት ዘመን ዕድገት ክብካቤ ማዕከላት ከ 57 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ገለፁ

ችግሮች ያላቸውን ተጋላጭነት ለመቀልበስ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በመቅረፅና ተግባራዊ እያደረገ፤ በሂደቱም ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።
‎‎ከነዚህ ፕሮግራሞች መካከል ከመንግስትና ከልማት አጋሮች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት የሚተገበረው የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም አንዱና ዋነኛው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ፕሮግራም በተለይም በማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች በመሳተፍ ላይ ያሉ እናቶች እርግዝናቸው ከታወቀ ጀምሮ ህፃኑ 2 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ወደ ጊዜያዊ ቀጥታ ድጋፍ ተሸጋግረው ከቆዩ በኋላ ወደ ስራ ሲመለሱ የማህበረሰብ ዓቀፍ ስራ ተሳትፏቸውና የልጅ መንከባከብ ሃላፊነታቸውን በአንድ ላይ ለማስኬድ እንደሚቸገሩ ጠቅሰዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የቅድመ ልጅነት ዘመን ዕድገት ማዕከላትን (Early Childhood Development Center/ECD) መገንባትና ለማዕከላቱ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ግዢ በመፈጸም ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ሚኒስቴር መ/ቤቱ በቁሳቁስ ለማሟላት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም ደረጃቸው የጠበቁና ለህፃናት ማቆያ ማዕከላት ግልጋሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶቹን ግዢ በመፈፀም ለሲዳማ፣ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ለደቡብ ኢትዮጵያ፣ ለትግራይና ለኦሮሚያ ክልሎች ድጋፍ ማድረጉን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስታውቀዋል።
‎
‎

Please follow and like us: