“ሴቶች የመምራት እድል ከተሰጣቸው ለሀገር እድገት ጉልህ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክቱ  ያለፉት ሰባት ዓመታት ተሞክሮዎቻችን ፍንትው አድርገው አሳይተውናል “- ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የለውጡ ትሩፋት የሆኑ ሴት አመራሮች መድረክ ላይ እንደገለፁት መድረኩ የ2017 በጀት አመትን የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕቅዶች በአስደማሚ ውጤቶች የደመደመበትን ጊዜ ላይ ማካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል ።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፉት አመታት  ለስርዓተ-ፆታ እኩልነት እና ለሴቶች ማብቃት ላላቸው የማይናወጥ አቋምና ቁርጠኝነት ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሴቶች ሁሌም እንደሚኮሩባቸው ገልፀዋል። መድረኩም  በአገራችን የሚታዩትን የተዛቡ ትርክቶችና የአገረ መንግስት ግንባታ ተግዳሮቶች በማረም ሂደት የራሱን አስተዋፆኦ የሚያበረክት ከመሆኑም በላይ የውይይት ባህልን በመጎልበት፣ ትብብር እና የልምድ ልውውጥን በማድረግ የአገራችንን ሴት ከፍተኛ አመራሮች አቅም በሚገባ ለመጠቀም እና የሚያሰችል ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል።

ሴቶች የመምራት እድል ከተሰጣቸው ያላቸውን እምቅ አቅምና ተሰጥዖ፤ እውቀትና ክህሎት በሚገባ አውጥተው መጠቀምና በመረጡት መስክ መስራት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ከመለወጥ ባለፈ ለማህበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ እና ለሀገር እድገት ጉልህ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አመራርነት ለሴቶች የተሰጠው ቦታ እና ያለፉት ዓመታት ተሞክሮዎቻችን ፍንትው አድርገው አንደሚያሳዩም ጠቁመዋል።

 

Please follow and like us: