Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ዩኤን ኤፍ ፒ ኤ /UNFPA/ ኢትዮጵያ ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውና ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት መረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማዘመን የሚያስችሉ የአይሲቲ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ
የቁሳቁስ ድጋፉን የዩኤን ኤፍ ፒ ኤ (UNFPA) ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ኮፊ ኩዋሜ ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል።
በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ አትዮጵያ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን ለመከላከል የሚያግዙ ፕሮግራሞችንና ልዩ ልዩ የአሰራር ማዕቀፎችን በመቅረፅ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል። ጥቃትን የተመለከተ የተጠናከረ መረጃ ለማደረጃት፣ የተጎጂዎችን መረጃ ሚስጢራዊነት ለመጠበቅ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈንና አገልግሎት አሠጣጥ ለማቀላጠፍ አሰራሩን ማዘመንና በዲጂታል ቴክኖሎጂን መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

የቁሳቁስ ድጋፉም በአማራ፣ በትግራይና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በፓይለት ደረጃ በተመረጡ 98 ተቋማት ላይ ስራውን ለማስጀመርና ውጤታማ ለማድረግ ጉልህ አስተዋፅዖ እንዳለው ተናግረዋል። ለተደረገው ድጋፍ ክብርት ሚኒስትሯ አመስግነው ወደፊትም አጋርነት የበለጠ በማጠናከር የመረጃ ስርዓቱን ለማስፋፋት፣ ተቋማዊ ለማድረግና ዘላቂ እንዲሆን ለማስቻል የክትትል ስራ ይሰራል ብለዋል።
የዩኤን ኤፍ ፒ ኤ(UNFPA) ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ኮፊ ኩዋሜ በበኩላቸው፥ ድርጅቱ በስነተዋልዶ ጤናና በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት እንዲሁም ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊትን መከላከል ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞችን ቀርጾ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የዩኤን ኤፍ ፒ ኤ(UNFPA) ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ኮፊ ኩዋሜ በበኩላቸው፥ ድርጅቱ በስነተዋልዶ ጤናና በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት እንዲሁም ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊትን መከላከል ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞችን ቀርጾ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።Please follow and like us: