Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 500 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 500 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ትላንት እና ዛሬ በተደረገ 2 ዙር በረራ የተመለሱት 108 ወንዶች፣ 373 ሴቶች እና 19 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 45 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡ መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 1 ሺህ 546 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
Please follow and like us:
