ለሀገራቸውና ለማህበረሰቡ ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አረጋውያን መብቶች መጠበቅና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላል- ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

‎አለም አቀፉ የአረጋውያን ቀን በሀገራችን ለ34ኛ ጊዜ “ለአረጋውያን ደህንነት መጠበቅ ሁለንተናዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ መርሐግብሮች ሲከበር ውሏል።
‎በዓሉን አስመልክተው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዛሬዎቹ አረጋውያን ዘርፈብዙ ተግባራትን የሰሩ የአገርና የትውልድ ባለውለታ በመሆናቸው የላቀ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። አረጋውያን በእድሜ መግፋትና በጤና መታወክ፣ በሉላዊትና በከተሞች መስፋፋት፣ በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ክስተቶች ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተጋላጭ የሚሆኑበት አጋጣሚ የሰፋ መሆኑን አንስተዋል። እንዲሁም እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ በመምጣቱ የተነሳ አረጋውያን በማምሻ እድሜያቸው ሲቸገሩ ይስተዋላል ብለዋል።
‎እውነታውን መገንዘብ ብቻ አይበቃም ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ መብቶቻቸውን በማክበር፣ ተገቢውን ክብርና ፍቅር በመስጠት ብሎም ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ሁሉም የዜግነት ሃላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል። ‎ሚኒስቴሩ ለሀገራቸውና ለማህበረሰቡ ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አረጋውያን መብቶች መጠበቅና ሁለንተናዊ የልማት ተካታችትና ተጠቃሚነት የተጀመሩ ስራዎችን ወዲፊትም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ለስኬታማነቱ የባለድርሻና አጋር አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልፀው እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፤ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል። የበዓሉ መከበር በአረጋውያን መብቶች ዙሪያ የህብረተሰቡንና ግንዛቤና ተሳትፎ ለማሳደግ ብሎም ጉዳያቸው ትኩረትና ምላሽ እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

Please follow and like us: