በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 602 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 602 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 10 ዙር በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 2ሺህ 040 ወንዶችና 532 ሴቶች እንዲሁም 30 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 97 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል። ‎ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 6 ሺህ 284 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎

Please follow and like us: