Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
አለም አቀፍ የታዳጊ ሴቶችና የ16ቱ የፀረ ፆታ ጥቃት ያለመታገስ ቀናት ሲከበሩ ለውጥ በሚያመጡ ተግባራት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ተጠየቀ፡፡
ይህ የተገለፀው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከአውሮፓ ህብረት፣ አየርላንድ፣ ኦስትሪያ አምባሳደሮችና፣ የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ ተወካዮች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት በሴቶች እና በሴቶች ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን ስናከብር ሀብት በማሰባሰብና አለም አቀፍ ግንዛቤን ከማሳደግ ባሻገር በተግባር ለውጥ በሚያመጡ እንቅስቃሴዎች ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡ በተለይም አለም አቀፍ የታዳጊ ሴቶችና የ16ቱ የፀረ ፆታ ጥቃትን ያለመታገስ ቀናቶች ሚኒስቴር መ/ቤቱ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ችግር ውስጥ ያሉ ታዳጊ ሴቶችንና ሴቶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል፡፡
ተወካዮቹ በበኩላቸው ስትራቴጂክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡ሁለቱን አለም አቀፍ ሁነቶችንም በጋራ ለማክበር ስምምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
Please follow and like us:
