Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የፀረ ሰው ፈንጂ ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጠውን ድጋፍ ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ (Survivors Recovery andRehabilitation Organization (SRaRO) ጋር በመተባበር ባዘጋጀውየምክክር መድረክ ላይ እንደተገለጸው የጸረ ሰው ፈንጂ ተጎጂ የሆኑ ሰዎች የሚሰጠውን ድጋፍ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈጻሚ ተወካይአቶ ሲሳይ ጥላሁን በእለቱ እንደገለጹት የፀረ-ሰው ፈንጂዎች መጠቀም፣ ማምረት፣ ማዘዋወር እንዲሁም ማከማቸትን የሚከለክለውን ዓለም አቀፍ ስምምነት መሰረት በማድረግ የጸረ ሰው ፈንጂ ተጎጂ ለሆኑ አካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን ድጋፍ በዘላቂነት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በጸረሰው ፈንጂ ተጎጂ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የተደራጀ መረጃ በማሰባሰብ ኢትዮጵያ በጸረ ሰው ፈንጂ ስምምነትመሰረት ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚቀርበው ሪፖርት በአግባቡ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አባይነህ ጉጆ በበኩላቸው የጸረ ሰው ፈንጂ ተጎጂ የሆኑ አካል ጉዳተኞችን በዘላቂነት የመንከባከብ ጉዳይለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የጋራ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተገንዝበው ወደ ተግባር መግባት አለባቸው ብለዋል። በየጸረ ሰው ፈንጂ ተጎጂ አካል ጉዳተኞችን ዘላቂ ተሳትፎና ተጠቃሚነትከማረጋገጥ ባሻገር በአለም አቀፍ ደረጃ የሚኖረንን መልካም ገጽታ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን የጠቀሱት የጸረ ሰው ፈንጂ ተጎጂ የሆኑ አካል ጉዳተኞችን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግየተቋቋመው መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት (SRaRO) ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በቀለ ጎንፋ ናቸው፡፡
