ኢትዮጵያ በማህበራዊ ደህንነትና ጥበቃ እንዲሁም ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የህንድን ልምዶችን እንድትጋራ ጥሪ

በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ’የህንድ ጤና አጠባበቅ እና ደህንነት’ ላይ ያተኮረ ፎረም በኤምባሲው አካሂዷል።
‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሁለቱ ሀገራት ባህል፣ በታሪክና በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ረጅም ጊዜን የስቆጠረ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀዋል። የሁለትዮሽ ትብብሩ እያደገ መምጣቱን ገልፀው፥ ፎረሙ በማህበራዊ ደህንነትና ጥበቃ እንዲሁም በጤና አጠባበቅ ረገድ ከህንድ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል እድል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

‎ጤና እና የተመጣጠነ ምግብ ለአገር ልማት መሰረት ናቸው ሲሉ የገለጹት ክብርት ሁሪያ አሊ እነዚህ መሰረታዊ መብቶች ለሁሉም ዜጎች በተለይም ለሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች እንዲሁም ለማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች እንዲደርሱ በማድረግ ረገድ ኢትዮጵያ ውጤታማ ስራዎች እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‎ሚኒስቴሩ እየተተገበሩ ያሉ ፖሊሲዎች አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና ሴቶችን ጨምሮ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን መደገፍ የሚያስችል አሰራር ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል።

‎በተጨማሪም በንጽህና፣ በተመጣጣነ የአመጋገብ ስርዓት እና በጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎች ላይ ያተኮሩና በህብረተሰቡ የተደገፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰራ መሆኑ ለዘላቂ ደህንነት እና ማህበራዊ ለውጥ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‎በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር በበኩላቸው ኢትዮጵያ በማህበራዊ ደህንነትንና ጥበቃ እንዲሁም ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የህንድን ልምዶችን እንድትጋራ ጥሪ እቅርበዋል፡፡

Please follow and like us: