የቤተሰብን መብትና ደህንነት ለማጠበቅ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ውጤት እንዲያመጣ በዘርፉ የሚሰሩ አካላት በቅንጅት እንዲረባረቡ ጥሪ ቀረበ

‎የቤተሰብን መብትና ደህንነት ለማጠበቅ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ውጤት እንዲያመጣ በዘርፉ የሚሰሩ አካላት በቅንጅት እንዲረባረቡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ጥሪ አቀረቡ።
‎‎በቤተሠብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ ከሚሰሩ የሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችል የጋራ ፎረም ተመስርቷል። በጋራ ፎረሙ ምስረታው ላይ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ፥ ቤተሰብ ትውልድ የሚገነባበት የህብረተሰብ መሰረታዊ ተፈጥሯዊ መነሻና ትልቅ ማህበራዊ ተቋም በመሆኑ ልዩ ጥበቃና ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል ብለዋል። ለዚህም መንግስት አደረጃጀት በማቋቋም፣ የአሰራር ማዕቀፍ በመቅረፅና የማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን በማስፋፋት በዘርፉ የሚጨበጥ ውጤት ለማስመዝገብ በሰፊው እየሰራ ስለመሆኑ ገልፀዋል። ከመንግስት ጥረት ጎን ለጎን ለችግር ተጋላጭ ቤተሰቦችን ለመርዳትና የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ የበኩላቸውን እየተወጡ ላሉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

 

‎ሆኖም በውስጣዊና ውጪያዊ ምክንያቶች ለሚያጋጥሙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት፣ የቤተሰብ መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ፣ በጎ እሴቶችን ለማሳደግ እንዲሁም ሀለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ሚናውንም በአግባቡ መወጣት እንዲችል በዘርፉ የሚሰሩ አካላት የጋራ ጥረትና ርብርብ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ‎የፎረሙ እውን መሆን የቤተሰብ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ መልካም አፈፃፁሞችን ለማስፋፋት እንዲሁም ክፍተቶቸን ለመሙላትና ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንደሀገር የሚደረገው ጥረት ወጥ፣ ዘላቂ ብሎም በተደራጀና ስርዓት ባለው መልኩ እንዲመራ ለማስቻል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ተብሏል።

Please follow and like us: