በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 402 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 402 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
‎‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 10 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 227 ወንዶች እና 164 ሴቶች እንዲሁም 11 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 92 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።‎ ‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
‎መስከረም 5/ 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 10 ሺህ 987 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎

Please follow and like us: