Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ዘላቂ፣ለችግርና ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
የህብረት ባንክ በበጀት ዓመቱ ባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቅጣት (የግዴታ ሰደቃ) የተሰበሰበ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ለ10 በጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ በትላንትናው ዕለት አበርክቷል፡፡

በዕለቱ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለጹት ባንኮች በሃገራችን በኢኮኖሚው ዘርፍ ከሚያደርጉት አስተዋጻኦ ጎን ለጎን የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ ሲሆኑ በዚህ ረገድ ህብረት ባንክ ያደረገው ድጋፍ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡ ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ የማህበራዊ ኃላፊነታቸውን (corporate Social Responsibility) በተገቢው የሚወጡ የፋይናንስ ተቋማት የሚጫወቱት ሚና በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡
ከእነዚህ ተቋማት መካከል ዋነኞቹ የሆኑት ባንኮች የፋይናንስ ተቋማት ሲሆኑ የፋይናንስ አቅርቦት አማራጭ በመሆን የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን በመደገፍና የልማት ፕሮጀክቶችን በማሳለጥ ለሃገር ኢኮኖሚ የሚያበረክቱት ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ዘላቂ፣ለችግርና ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ ጥሪ
