ተተኪ ሴት አመራሮችን ለማፍራት ያለመ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዩ ኤን ውሜን /UNWomen/ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት ተተኪ ሴት አመራሮችን ለማፍራት ያለመው 2ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።

‎‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የሚኒስቴሩ የህፃናት መብት መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዘቢደር ቦጋለ እንደገለፁት፥ የሴቶችን የአመራርነትና ውሳኔ ሰጪነት አቅምን ማሳደግ ለሀገር ሁለተናዊ እድገት ከፍተኛ ጥቅም አለው። ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማምጣት የሴቶችን የአመራርነት ቁጥር ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህም ሚኒስቴሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሴቶች አመራርነት ሚና ለማሳደግ እንደ ሀገር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ‎አመራርነት ችግርን መፍታት፤ ህዝብን ማገልገል ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ለአመራርነት እንዲበቁ ማድረግ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ‎የሚሰጠውን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ስልጠና በጥሞና እንዲከታተሉና እውቀቱን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ‎ተተኪ ሴት አመራሮች ለማፍራት እንዲያስችል በቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሣለወርቅ ዘውዴ ኢኒሼቲቭ በ2014 ዓ.ም ስልጠና መሰጠት የተጀመረ መሆኑ ለትውስታ ተጠቅሷል።

‎‎የዩኤን ውመን ኢትዮጵያ ሀገራዊ ፕሮግራም ተወካይ ሚስተር ሻድራክ ዱሳቤ በበኩላቸው፥ ድርጅቱ ለሴቶች መብት መከበር፣ ለስርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ለማብቃት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንና በቀጣይም ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። ‎ስልጠናው ለቀጣይ አስር ተከታታይ ቀናት እንዲሚሰጥ የወጣው መርሐግብር ያመለክታል።
‎

Please follow and like us: