Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 406 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 406 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 11 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 959 ወንዶችና 407 ሴቶች እንዲሁም 40 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 56 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 18 ሺህ 224 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
Please follow and like us:
